Saturday, 18 January 2025
Loading Events

« All Events

  • This event has passed.

የሃዘን መግለጫና አገራዊ ጥሪ: ከ 17 ድርጅቶች የተሰጠ መግለጫ

July 1, 2020 @ 8:00 am - 5:00 pm

የሃዘን መግለጫና አገራዊ ጥሪ:

ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ/ም ቀን

እኛ ስማችን ከታች የተዘረዘረው ድርጅቶች፤

ዝነኛውና ተወዳጁ ወጣት ድምጻዊ ወገናችን አቶ ሃጫሉ ሁንዴሳ ትላንት ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም የመገደሉን ዜና የሰማነው በታላቅ ሃዘንና ብስጭት ነው። የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን ለባለቤቱ፣ ለልጆቹ፣ ለመላው ቤተሰብና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንገልጻለን።

አገራችን ከባድ ፈተናዎች በተጋረጡባትና የልጆቿን የጠነከረ አንድነት በምትሻበት በዚኽ ጊዜ የተፈጸመ ይኽ የወንጀል ድርጊት በወጣቱ ድምጻዊ ወገናችን ላይ ብቻ የተቃጣ ሣይሆን በአገራችን አንድነት፣ በሕዝባችን ሰላምና በአብሮነታችን ላይ የተሰነዘረ ጥቃት አድርገን እንቆጥረዋለን።

ስለሆነም፣

  1. መንግሥት ይኽን ወንጀል የፈጸሙትንና ከኋላ ሆነው የተባበሩና ያስተባበሩትን ጊዜ ሳይወስድና የቅርብም ሆነ የሩቅ ጠላቶቻችን እንደሚያስቡትና እንደሚፈልጉት አገራችን ለቀጣይ ችግር እንዳትዳረግ በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲያደርጋቸው፤
  2. ማዕከላዊ መንግሥት በዚኽ ሰበብ ሕዝብን እርስ-በርስ ለማናከስ በሚደረግ ሰበካ በስሜት በመገፋት በሰው ሕይዎትና በንብረት ላይ ጥፋት እንዳይደርስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኮቪድ-19 ምክንያት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማጠናከር ጭምር ሕግና ሥርዓት የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣና አገርና ሕዝብን እንዲያረጋጋ፤
  3. በእንደዚኽ ዓይነት የቀውጢ ጊዜ አንድነታችን እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ከፖለቲካ ድርጅቶች ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የጋራ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ በአክብሮት እናሳስባለን።

ኢትዮጵያ በአንድነቷ ፀንታ ለዘላለም ትኑር

 

መግለጫውን የፈረሙት ድርጅቶች፤

  1. Consortium of Ethiopian Civil Society Organizations (TIBIBIR)
  2. Ethiopian Advocacy Network
  3. Ethiopian-American Civic Council
  4. Ethiopian International Professional Support for Abbay
  5. Ethiopian Waters Advsory Council (EWAC)
  6. Ethiopiawinnett: Council for the Defense of Citizens Rights
  7. Ethiopian Community Association of Chicago, Inc.
  8. Ethiopian Community and Cultural Center of Bay Area
  9. Ethiopian Community Center of Las Vegas, Nevada
  10. Ethiopian Professional Association in Southern Africa
  11. GERD Support Group in Arizona
  12. GERD Support Group of Los Angeles
  13. GERD Support Group in Oregon and South-Western Washington
  14. Forum 65 (www.65Percent.org)
  15. Global Alliance for the Right of Ethiopians (GARE)
  16. Network of Ethiopian Scholars
  17. Vision Ethiopia

Details

Date:
July 1, 2020
Time:
8:00 am - 5:00 pm
Event Tags:

Registrations are closed for this event