____________________________________________________________________________
ለ PDF ኮፒ እዚህ ላይ ይጫኑ (Click here for PDF version)
March 13, 2023
የዘረኛው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ በሕዝብ ትግል ተገርስሶከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ በዐብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ መሪነትበአማራው ላይ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሙማ የዘር ማጥፋት ዘመቻዛሬ ወደ ሌሎች ክፍሎች ተስፋፍቶ፣ የጉራጌ፣ የሲዳማ፣ የወላይታ፣የቤኒሻንጉል፣ የሱማሌ፣ የጋምቤላና ሌሎች ወገኖቻችንም በአሰቃቂሁኔታ እየተጠቁ፣ ንብረታቸው እየተዘረፈና ሰላማዊ ነዋሪዎችእየተጨፈጨፉ ይገኛሉ::
በዘር ማጥፋት፣ በታሪክ ክለሳ፣ በባህል ምረዛ፣ በሃይማኖት ብረዛ፣ በሃብት ዝርፊያና በእርስት ቅሚያ ላይ የተመርኮዘው፣ የኦሮሙማኋላ ቀርና ስግብግብ ስርአት፣ አገሪቱን እያናወጠ ይገኛል::
በቅርቡ በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና በኦርቶዶክስቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ላይ የተነጣጠረ የከፋፍሎ ማዳከምናየማፈራረስ ዘመቻ አካሂዶ አገሪቱን እንደ ድርና ማግ ያስተሳሰሯትንእሴቶች በተቀነባበረ ስልት እየበጣጠሰ ይታያል።
በይበልጥም፣ በአረሜኔያዊ ድንቁርናው ታውሮ፡ ከኢትዮጵያ አልፎለመላው ጭቁን ሕዝብ መመኪያ በሆኑ ቅርሶችና የምርምርመሰረቶች ላይ ከመጠን ያለፈ ጉዳት አድርሷል::
የመላው ሕዝብ መግባቢያ ቋንቋ የሆነውንና የፅሁፍና የምርምርመሣሪያነቱ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተደናቂነት ያስመዘገቡትንየአማርኛ ልሳንና የግእዝ ፊደልን አግዶና በአብዛኛው የአገሪቱክፍል በትምህርት ደረጃ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አድርጓል::
የጥቁር ሕዝብ ነፃነት መንፀባረቂያና መመኪያ የሆነውን የአድዋድል በአል በአግባቡ እንዳይከበር በተደጋጋሚ አስተጓጎሎአል፣ ይባስብሎም በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በአማኞችና የአድዋበአል ኣክባሪዎች ላይ ፋሽሽታዊ እርምጃ በመውሰድ አስከፊ የታሪክጥቁር ነጥብ አስፍሮአል።
የአዲስ አበባ ከተማን አስተዳደር በኦርሙማ አክራሪ መሪዎች እጅአስገብቶ፣ ብዙውን የከተማይቱን ክፍል ወደ ኦሮሚያ ክልልአስተላልፎአል። ከዚያም በላይ፣ ወደ መዲናይቱ መግቢያ የሆኑየአካባቢ መንደሮችን “ሸገር” በሚል ስያሜ አደራጅቶ በመቆጣጠርላይ ይገኛል። ወደ አዲስ አበባ በነፃነት የመግባትና የመውጣትእድልን ዘር እየመረጠ ያግዳል፤ በተለይም አማሮችን እየመረጠይከለክላል። ከዚህም አልፎ፣ የኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች፡በተለይምየአማሮችን የመኖሪያ ቤቶች እያፈረስ ተከላካይ የሌላቸውንወገኖቻችንን መጠጊያና መጠለያ አጥተው እንዲሰቃዩ አድርጓል::
በወለጋ፣ ሰሜን ሸዋና ተመሳሳይ ቦታ ነዋሪ የነበሩትን በሚሊዮኖችየሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ከቀያቸው አፈናቅሎ፣ በአስር ሺዎችየሚቆጠሩትን ፈጅቶ ሲያበቃ፣ አሁን በጉራጌና በሌሎች ወገኖችላይ ተመሳሳይ የሕግ አልባና የወንጀለኛ ድርጊቶችን እየፈፀመይገኛል::
ኢትዮጵያዊነቱን በጽኑ የሚያምነውን የደቡብ ክልል ለኦሮሙማበላይነት በሚያመች መንገድ በማፈራረስና ከፋፍሎ እያዳከመይገኛል። የራሳቸውን ክልል የመመስረት ጥያቄ ያቀረቡትን እንደጉራጌና ወላይታ ላሉት ዜጎቻችን ለጥያቄቸው መልስ መስጠት ቀርቶመብታቸውን ለማስከበር ሰላማዊ ሰልፍ እንኳን እንዳያደርጉናድምጻቸዉን እንዳያሰሙ እየታፈኑ፤ ከሥራ እየተባረሩ የእስር፣የድብደባና የእንግልት በደል እንዲደርስባቸው ሆነዋል።
በተለይም ሰሞኑን በወልቂጤና ሌሎች አካባቢዎች በሚኖረውየጉራጌ ሕዝብ ላይ እየደረሰ የሚታየው ከፍተኛ ዝርፊያ፣ ግድያናእስራት የዚህን አስተዳደር ኋላቀርና ጨካኝ አረመኔያዊ ገፅታበጉልህ የሚያሳይ ማስረጃ ሆኖ ይቆጠራል። የዞኑን በጀት ለደቡብልዩ ኃይልና ለፌዴራሉ ኃይል አፈና ማስፈፀሚያ በማድረግ፣ ውሃፍለጋ ጀሪካን ይዞ የወጣው ሰላማዊ ሰው እስከመገደል ጥቃትደርሶበታል። የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የሕዝብ ምክር ቤት ተመራጮች፣ ነፍሰጡርና የቤት እመቤቶች ሳይቀሩ የህክምና እርዳታ እንዳያገኙ ተከልክለው፣ በእስር ቤት እንዲማቅቁ ተደርገዋል።
ቀደም ሲል የአማራውን ሕዝብ ለማዳከም ባለው እኩይ አላማ፣ክልሉን ለሕወሓትና ለሰሜን ሱዳን አጋልጦ እንዳስጠቃ ሁሉ፣ ዛሬደግሞ የጋምቤላን መሬት በደቡብ ሱዳን አስወርሮ፣ የወገናችንኃብት እንዲዘረፍ፣ እርስቱ በውጭ ወራሪ ኃይል እንዲነጠቅናሕዝቡም በባእድ ጦር እንዲሰቃይ አድርጓል::
“ሁሉም የእኔ” በሚል የነጣቂ መንፈስ የተለከፈው የኦሮሙማስርአት፣ ሰሞኑን ትኩረቱን ወደ ታላቁ የአባይ ግድብ (GERD) አዙሮ፣ለዓመታት የዘር ማፅዳት ዘመቻ በአማራው ላይ ሲያካሄድበትበነበረው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላይ የተስፋፊነት ጦሩንእያዘመተ ይታያል::
ቪዥን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ እንዳስገነዘበው፣ በዐብይ አህመድናሽመልስ አብዲሳ መሪነት ኢትዮጵያን እያፈራረሰ፣ ነዋሪወቿንእየጨፈጨፈና እየዘረፈ የሚገኘውን የኦሮሙማን ፋሽሽታዊስልቀጣ መግታት የሚቻለው በተቀነባበረና በተናበበ ሕዝባዊትግል ብቻ መሆኑን አጥብቆ ያምናል:: ስለሆነም ወገኖቻንን ከከፋችግርና እልቂት ለመታደግና አገራችንንም ከተደቀነባት አደገኛቀውስ ለማዳን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የትግል ስልቶችበመጠቀም ይህን ዘረኛ ስርዓት መታገል የግድ ይሆናል። ለዚህምየህልውና ትግል ጥሪ በድጋሚ ያቀርባል::
- በአገር ውስጥ የሚገኙ ተጠቂ ዜጎቻችን በሙሉ በሰላማዊሰልፍ፣ በሥራ ማቆም አድማ እና ሌሎችም የኦሮሙማንየጭቆና አገዛዝ በሚጎዱ ሰላማዊ መንገዶችባለማቋረጥ ተቃውሟቸውንና እምቢተኝነታቸውን መግለፅ::
- በውጭ የሚኖሩ ፍትህ-ወዳድ ወገኖች፣ የኦሮሙማ የጭቆናአገዛዝ የገንዘብ ምንጭ የሆኑትን መንገዶች ሁሉ ማድረቅ::በተለይም የአገዛዙን ጨካኝና አደገኛ ባህሪ ዓለም አቀፋዊእውቅና እንዲያገኝ በማድረግ የውጭ እርዳታ ማእቀብማስደረግና እንደ ኢትዮጵያ አየር መንግድ ያሉትን የዘረኛውመንግሥት የገንዘብ ምንጮችን መጠቀሚያ አለማድረግ::
- በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ኃይሎች የጋራየትግል መርሀግብር በአስቸኳይ ነድፈው፣ በዲሞክራሲያዊአሠራር ላይ የተመረኮዘ አንድነትን መፍጠር:: በተለይምየአማራው ክፍል በአንድነት ቆሞ፣ አሁን በመጠቃት ካሉትወገኖቹ ጋር ኃይሉን በማቀናጀት፣ የራሱን ህልውናና የወገኖቹንደህንነት ለመከላከል በቁርጠኝነት መነሳት::
- በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ ምሁራንና የተለያዩ የሀይማኖትተከታዮች፣ በኦሮሙማ እየተካሄደ የሚታየውን የታሪክ፣የእምነትና የባህል ማጥፋት ዘመቻ በሚቻለው መድረክ ሁሉአጥብቆ መዋጋት::
- በመጨረሻም፣ ዐብይ አህመድ፣ ሽመልስ አብዲሳናጭፍሮቻቸው በተከታታይ የፈፀሙትን ፋሽሽታዊ ወንጀልለፍርድ አቅርቦ፣ ወንጀለኞቹ ለተግባራቸው ተመጣጣኝ የሆነዓለማቀፋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረግ::
ከላይ የተዘረዘሩትን የትግል ስልቶች ተግባራዊ ለማድረግ በቂኃይልና አስተማማኘ ነባራዊ ሁኔታ አለ ብሎ እያመነ፣ ቪዥንኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ትጋትና አለመሰልቸት ከጭቁንወገኖቹ ጋር በመሰለፍ፣ በዘር ላይ የተመረኮዘውን አረመኔያዊአገዛዝ ለመታገል ጠንክሮ እንደሚሠራ እንደገና ያረጋግጣል::
ከቪዥን ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ
Page | 1 of 2