በወቅታዊ የኢትዮጵያ ቀውጢ ችግሮች ላይ የተሰጠ መግለጫ
ራዕይ ለኢትዮጵያ (Vision Ethiopia)፣ ወገንተኛ ያልሆነ የኢትዮጵያ ምሁራንና ባለሙያዎች ማሕበር፣ በኦሮሞ ጽንፈኞችና በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ መንግሥት እውቅናና ድጋፍ እየተፈጸመ ያለውን፣ በብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አጥብቆ ያወግዛል።
በመላ አገሪቱ እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት ጥቃትና የኦሮሙማ እንቅስቃሴ ተስፋፊ ኃይል መጠናከር ሊሳካ የቻለው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መንግሥት እውቅናና ተባባሪነት ብቻ እንደሆነ ራዕይ ለኢትዮጵያ አጠንክሮ ያምናል።
ናዚ ጀርመን በአይሁዶች፣ እንዲሁም ፋሽስት ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ እንደፈጸሙት፣ ወይም በቅርብ ዘመን በሩዋንዳ ኢንተርሃውሜ እንደታየው የዘር ፍጅት፣ መንግሥት ራሱ የተግባሩ ተካፋይ ካልሆነ በስተቀር፤ በኢትዮጵያ ዛሬ በመካሄድ ላይ ያለዉን፣ ሕዝብ በማንነቱ ሲገደልና ከአጽመ-ርስቱ ሲፈናቀል፣ አይቶ እንዳላየ በግድየለሽነት የታገሰ መንግሥት በሰው ልጅ ታሪክ ኖሮ አያውቅም።
በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በረጅም ታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የህልውና ሥጋት ገጥሟት ይታያል። ባለፉት ብዙ መቶ ዘመናት ከተደጋጋሚ ጥቃቶች የተረፈች አገር፤ በ16ኛው ክፍለዘመን የኢማም አሕመድ ኢብራሂም አል-ጋዚ ን ጥፋት፤ ቀጥሎም የተስፋፊ ኦሮሞ ወረራ ንና በ 1930ዎቹ የጨካኙን ፋሺስት ጦርነት የተቋቋመች አገር፣ እንደገና ከውድቀት አፋፍ ላይ ደርሳ ትታያለች።